1. ይዘት
  2. ቀዘፋ
  3. ተጨማሪ ይዘቶች
  4. አብሮ መቅዘፍ
  5. ፍለጋ
  6. ከ 30 ቋንቋዎች ይምረጡ።

 
 
 

 

 | 03.12.2008 | 14:00 UTC

ብራስልስ፡ የኔቶ ስብሰባና ሩስያ

የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ኪዳን፡ ኔቶ አባል ሀገሮች ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ከሩስያ ጋር ተቋርጦ የነረውን ውይይት ቀስ በቀስ ለመጀመር በእብራእስስ ስብሰባቸው ላይ ተስማሙ። ሩስያ ጎረቤት ጂዮርጅያን የወረረችበትን ድርጊት በመቃወም ነበር ኔቶ ባለፈው መስከረም ወር ከሞስኮ ጋር ውይይቱን ያቋረጠው። ሩስያ ምንም እንኳን ከአጭሩ የጂዮርጅያ ወረራ በኋላ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ደምብ ሙሉ ለሙሉ ባለማክበርዋ አሁንም ቅሬታ ቢኖርም፡ ይፋ ያልሆነውን ውይይት እንደሚጀመር ኪዳኑ አረጋግጦዋል። ይሁንና፡ ሩስያ ለጂያዮርጅያ የግዛት ሉዓላዊነት እውቅና እስካልሰጠች ድረስ ኪዳኑ አሁን ከሩስያ ጋር ለመቀራረብ የደረሰውን ውሳኔ የኔቶ አባል የሆኑት የምስራቅና የማዕከላይ አውሮጳ ሀገሮች እንደማይደግፉ አንድ የኔቶ ዲፕሎማት አስታውቀዋል። ጀርመን፡ ፈረንሳይና ሌሎቹ አባል ሀገሮች ውይይቱ በቅርቡ የሚጀመርበትን ሀሳብ ደግፈዋል። የኔቶ ዋና ጸሀፊ ያፕ ደ ሆፕ ሼፈርም ከሩስያ ጋር ያለው የኪዳኑ ግንኙነት እንዲሻሻል ያላቸውን ፍላጎት አጉልተዋል።

« ከካውካሰሱ ውዝግብ በኋላ ከሩስያ ጋር መደበኛው ውይይት ሊቀጥል እንደማይችልና ግንኙነታችንን በሚገባ ማጤን እንዳለብን ነበር የወሰነው። ዛሬም ስለግንኙነቱ ማሰላሰላችንን በመቀጠል ወደፊት ከሩስያ ጋር ስሚኖረው ትብብር እንመክራለን። ዓላማችን በፍጹም ተቀይሮ አያውቅም፡ አንድ የሆነች፡ ነጻና ሰላም የሰፈነባት፡ ሩስያም ኃላፊነት የታከለበት ዓቢይ ሚና የምትይዝባት አውሮጳን መገንባት ነው። »

ሀያ ስድስቱ የኔቶ አባል ሀገሮች ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ጂዮርጅያና ዩክሬይን በፍጥነት የኔቶ አባል ነትን እንደማያገኙ፡ በዚህ ፈንታ ከኪዳኑ ጋር ጠንካራ ትብብር የሚኖርበት ሀሳብ እንዲቀርብላቸው ወስነዋል። 

  



 

DW-TV EUROPE live

Journal (english) - With In Depth